vic_logo
coronavirus.vic.gov.au

ትምህርት (Education) - አማርኛ (Amharic)

በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅት በትምህርት ላይ ያሉ ለውጦች እና ለወላጆች እና ለአሳዳጊዎች የሚሰጥ ድጋፍ።

ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ በትምህርት - መረጃ ለወላጆች፣ ለተማሪዎች እና ለአስተማሪዎች ገጻችን [Education – information for parents, students and educators page] ማግኘት ይችላሉ። 

በቋንቋዎ የበለጠ እገዛ ከፈለጉ በTIS National በ131 450 በመደወል አስተርጓሚ መጠየቅ ይችላሉ ከዚያም በ1800 338 663 ከኮሮናቫይረስ (ኪቪድ-19) የስልክ መስመር ጋር እንዲያገናኝዎት ይጠይቁ።

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ጊዜ ልጆችዎን ስለማነጋገር (Talking to your child during coronavirus)

ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ልጅዎን ለማነጋገር ይህ መመሪያ ይረዳዎታል። እንዲሁም እንዴት ደህንነቱን መጠበቅና የተረጋገጠ ንግግር ማድረግ እንደሚቻል ምክሮችን በማቅረብ ከሚረዱ መገልገያ ምንጮች ጋር በማገናኘት ይረዳል።

ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ለመነጋገር አለመፍራት

 • ብዙዎች ህጻናት ስለ ቫይረሱ ቀደም ሲል ስለሚሰሙ ታዲያ ወላጆችና ተንከባካቢዎች ስለ ቫይረሱ መነጋገሩን ማስወገድ የለባቸውም።
 • ስለ ሆነ ነገር አለመነጋገር ለህጻናት በበለጠ ሊያስጨንቅ ይችላል። በታመኑ ምንጮች የቀረቡትን እውነታ መግለጫ ጽሁፎች በማቅረብ ለልጅዎ እውቅና ስሜት ይረዳሉ። ከጓደኞች ወይም ማሕበራዊ መገናኛ ከሚሰሙት መረጃ ይህ የበለጠ ማረጋገጫ ነው።

የህጻን-ጓደኝነትን በእምነት መጠቀም

 • ስለ ልጅዎ እድሜ ማሰብ። በሚረዳቸው ቋንቋ በመጠቀም መረጃን ማቅረብ።
 • ለሁሉም ነገር መልስ መስጠት ካልቻሉ ምንም አይደል; የሚያሳስበው ግን ለርስዎ ልጅ መገኘቱ ነው።   
 • በተቻለዎት ሀቅነትና ግልጽ የሆነ መልስ መስጠት። በአንድ ጊዜ ብዙ መረጃ መስጠት ሊያበስጭ ስለሚችል ብዙ አለማካፈል።
 • ለልጅ በሚያነጋግሩበት ጊዜ ረጋ በማለትና በአወንታዊ ሆኖ ለመቆየት መሞከር።
 • ልጅዎ ብዙ ሊያስጨንቀው በሚችል መንገድ ምነጋገሩን ማስወገድ።

በልጅዎ በኩል መመራት

 • ልጅዎ ስለ COVID-19 ቫይረስ የሰማው ማንኛውም ነገር ካለ እንዲነግርዎ መጋበዝና እንዴት እንደሚሰማቸው ማየት።
 • ጥያቄዎች እንዲያቀርቡ እድሉን መስጠት። ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት መዘጋጀትና ከልጅዎ ጋር ያለውን ሁኔታ ማጣራት።
 • አንዳንድ ህጻናት ከራሳቸው ባሻገር ስለሌሎቹ በበለጠ ይጨነቃሉ። በተቻለ መጠን ተክኖሎጂ እንደ Facetime/ፌስ ታይም በመጠቀም ከጓደኞችና ቤተሰብ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማድረግ።

በድጋሜ ማረጋገጥ

 • ከልጆችዎና ከሌሎች ጋር በሚነጋገሩበት ጊዜ ስለሚጠቀሙበት ቋንቋ ማወቅ። ያስተውሉ ህጻናት የጎልማሳ አዋቂ ሰዎችን ንግግር ከመደበኛው ጊዜ በበለጠ ያዳምጣሉ።
 • የልጅዎን ፍርሃት ውድቅ አለማድረግ። ለነሱ እንደሚያስጨንቅ ይታወቃል ምክንያቱም ቀደም ሲል በእንደዚህ ዓይነት ላይ ልምድ ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል።
 • ስለ COVID-19 ቫይረስ በበለጠ ለመማርና የእኛን ደህንነት ለመጠበቅ፤ ሀኪሞችና ሳይንቲስቶች በሞላው ዓለም በከፍተኛ ሥራ ላይ እንዳሉ ለልጅዎ መንገር።

ደህንነትዎን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ማትኮር

 • ምን እየተፈጠር እንዳለ አንዳንድ የመከላከያ ዘዴዎችን ለእነሱ መንገር። ለማሕበራዊ እርቀት፤ እጅን መታጠብ እና እነዚህን በሚገባ እንዴት ማካሄድ እንደሚቻል ያለውን ጥቅም ማስተማር። በሚስሉበትና ሲያነጥሱ ሌሎች ሰዎችን ለመከላከል ሃላፊነት እንዳለባቸው ማስታወስ።
 • ህጻናት የፊት ጭንብል ማስክ አጥልቀው ላሉ ሰዎች ሲያዩ፤ እነዚህ ተጨማሪ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ናቸው ብሎ መንገር እንጂ በአሁኑ ጊዜ የፊት ጭንብል ማስክ ማጥለቅ ለአብዛኛው ሰው ጠቃሚ አይደለም።
 • እነሱ ወይም ቤተሰባቸው ደህና ካልሆኑ በስልክ 000 አድርገው እንዲደውሉ ማስታወስ።

ለመደበኛ ተግባር መለጠፍ

 • በቀናት ውስጥ ለመደበኛ የምግብ ጊዜያትና የአልጋ መኝታ ጊዜ ማቀናጀት ህጻናት ደስተኛና ጤናማ እንዲሆኑ ጠቃሚ ከሆኑት አንደኛው ክፍል ነው።
 • ከቻሉ በየቀኑ መደበኛ ተግባር እንዲኖርዎ ማድረግ። ከቤተሰብዎ ጋር ለሚጠቀሙት የጊዜ ሰንጠርዥ መፍጠርና ሁሉም ሰው ማየት በሚችልበት ፍሪጅ ላይ መለጠፍ/ማስቀመጥ።
 • እንደ ከቤት ውጭ ቆይታ ጊዜ፤ የጨዋታ ጊዜ፤ በተክኖሎጂ ላይ ነጻ ጊዜ፤ የመፍጠሪያ ጊዜና መማሪያ ጊዜን የመሳሰሉ ነገሮችን ያካትታል።
 • ልጅዎ በሚፈልገውና ስሜታዊ በሚሆንበት ጊዜ ምላሽ መስጠትና ተለዋዋጭ መሆን ይቻላል።

በቀጣይነት ማነጋገር

 • ልጅዎ እስካሁን ምን እንደሚያውቅ ወይም እንደሚያሳስበው ማጣራት። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ሰምተው ከሆነ ማጣራቱ ጠቃሚ ይሆናል።
 • አዎ/yes ወይም አይ/no የሚል መልሶች ለሌላቸው ጥያቄዎችን መጠየቅ።
 • ልጅዎ የሆነ ነገር ከጠየቅዎትና መልሱን የማያውቁት ከሆነ፤ አላቅም ማለት። ጥያቄውን በመጠቀም በጋራ ለመሆን እድል ማግኘት።
 • ልጆችዎ ፍላጎት ያላቸው የማይመስሉ ከሆነ ወይም ብዙ ጥያቄዎች የሚጠይቁ ከሆነ፤ ምንም አይደል።
 • ሁላችን ማዳመጥና መናገር እንዳለብን እንዲያውቁ ማድረግ ነው።

ከጥንቃቄ ጋር ለኮሮና ቫይረስ መቅረብ

 • ከተነጋገሩ በኋላ ታዲያ ልጆች በጭንቀት ላይ እያሉ ጥሎ አለመሄድ ጠቃሚ ነው።
 • የርስዎን ንግግር ከጨረሱ በኋላ የልጆችን መጨነቅ ስሜት ምልክቶች ማየት። ይህም በእነሱ አነጋገር ድምጽ፤ አተነፋፈስ ወይም የሰውነት ምልክት ቋንቋ ግንኙነት ለውጥ ሊሆን ይችላል።

በልጆችዎ ላይ መታየት ያለባቸው ነገሮች

Iበህጻናትና በታዳጊ ወጣቶች ላይ የመጨናነቅ ምልክት ማሳየቱ የተለመደ ነው። በተለመዱት ሁኔታዎች የሚካተት:

 • ፍርሃትና ጭንቀት
 • መበሳጨት፤ መጨናነቅና መደናገር
 • መተከዝ
 • ክህደት/መቃወም

እራዎን ለመንከባከብ ማስተዋል

 • የጭንቀት ስሜት እንዳለብዎት ካወቁ፤ ከልጅዎ ጋር ከመነጋገርዎ ወይም ለጥያቄዎች መልስ ከመስጠቱ በፊት እስኪረጋጉ ድረስ ለጥቂት ጊዜ መቆየት።
 • የጭንቀት መንፈስ ወይም የመረበሽ ስሜት ካለብዎት፤ ለልጅዎ መንገር ያለብዎ አንዳንድ መረጃ ፈልጌ ወዲያውኑ አነጋግርሃለሁ ማለት ነው።
 • እንዲሁም የሚከተሉት የውጭ መገልገያ ምንጮች ስላለዎት የአእምሮ ጢና እና ደህንነት ድጋፍ ያቀርባሉ:
  • headspace - ለቤተሰብና ጓደኞች ድረገጽ፡
  • Beyondblue – ለ COVID19 ድረገጽ፡
  • Lifeline - በCOVID-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ ለቤተሰብና ጓደኞች ድረገጽ፡

ተጨማሪ መገልገያ ምንጮች

ልጅዎን በሚያነጋግሩበት ጊዜ እርዳታ

 • Raising Children Network ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) እና በአውስትራሊያ ህጻናት ድረገጽ፡
 • Emerging Minds – በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ጊዜ ለህጻናት እርዳታ ድረገጽ፡
 • KidsHealth - ኮሮና ቫይረስ (COVID-19): ልጅዎን እንዴት እንደሚያነጋግሩ ድረገጽ፡
 • eSafety ቢሮ:
  • COVID-19 ቫይረስ: ትምህርት ቤቶችንና በመስመር ላይ ደህንነት ላለው መማር ስለመቀጠል
  • COVID-19 ቫይረስ: ለወላጆችና ተንከባካቢዎች በመስመር ላይ የተዘጋጀ ደህንነቱ የተጠበቀ

ከህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች ጋር አብሮ ለመጠቀም

 • headspace - ከኖቨል ኮሮና ቫይረስ በተዛመደ ጭንቀትን እንዴት መወጣት እንደሚቻል ድረገጽ፡
 • ReachOut - በኮሮና ቫይረስ ጊዜ ስለመቋቋም ድረገጽ፡

ወደ መዋእለ ህጻናት (ቻይልድ ኬር እና ኪንደርጋርተርን) ስለመመለስ (Returning to child care and kindergarten)

ከሰኞ ኦክቶበር 5 ጀምሮ

በሜትሮፖሊታን ሜልበር እና በሁሉም ከተማዎች እና በገጠራማው ቪክቶሪያ ያሉ ሁሉም ህጻናት ወደ ሚከተሉት መመለስ ይችላሉ 

 • ቻይልድኬር (ሙሉ ቀን ወይንም ፋሚሊ ደይ ኬር) እና
 • ባለ ክፍለ ጊዜ ኪንደርጋርተርን እቦታው ላይ በመሄድ መከታተል ይችላሉ።

ይህም የቪክቶሪያ መንግስት ቪክቶሪያን ለመክፈት እየወሰደወ ባለው ሶሰተኛው ደርጃ እርምጃ አካል ነው።

እነዚህ ለመክፈት የሚደርጉ እርምጃዎች በኮሮናቫይርስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስን መሰርት ያደርገ ነው። በቪክቶሪያ ዋና የጤና ኦፊሰር ምክር መሰርት ለውጦችን ልናደርግ እንችል ይሆናል።

ስለልጅዎ ደህንነት ሐሳብ ሊገባዎ እንደሚችል እንገነዘባለን። አሁን ባገኘነው ምክር መሰርት ቻይልድ ኬር እና ኪንደርጋርተርን ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ሲሆኑ ዝቅተኛ የኮሮናቫይርስ (ኮቪድ-19) ተጋላጭነት ያለባቸው ቦታዎች ናቸው።

ይህንንም የነገሩን

 • የቪክቶሪያ ዋና የጤና ኦፊሰር

እና

 • በAustralian Health Protection Principal Committee (AHPPC).

መንቀሳቀስ በታገደበት ወቅት ወደ ቻይልድ ኬር እና ኪንደርጋርተን ስለ መሄድ ለውጥ ተደርጎ ነበር። የዚህ ህግ ዋና አላማው በማህበርሰቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ የታቀደ ነበር። ይህ የተደርገው ቻይልድ ኬር እና ኪንደርጋርተን ለልጆች እና ለሰራተኞቹ ተገቢ ቦታ ስላልነበር አይደለም።

የልጅዎ ቻይልድ ኬር ወይንም ኪንደርጋርተን COVIDSafe እቅድ አለው። ይህም የጤና እና የደህንነት መጠበቂያ አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ያካትታል፣ ላምሳሌ ያክል ክፍሎችን እና መጫዎች እና መገልገያ እቃዎችን አዘውትሮ ማጽዳት።

ለሁሉም ህጻናት ወደ ቻይልድ ኬር ወይንም ኪንደርጋርተን መሄድ በጣም ጠቃሚ ነው። ለህጻናቱ እነዚህ ቦታዎች ለመማር እና ለማደግ ይርዱዋቸው ዘንድ የግድ መሄድ አለባቸው። በተለይም ደግሞ ህጻናት በ2021 ፕሬፕ የሚጀምሩ ከሆነ ለመዘጋጀት ይርዳቸዋል።  

ትምህርት ቤቶች በ2021 የፕሬፕ ተማሪ ህጻናትን ለመቀበል ዝግጁ ይሆናሉ (Schools will be ready for children starting Prep in 2021)

የርስዎን ቤተሰብ እና ልጅዎን በ2021 ወደ ፕሬፕ የምታደርጉትን ሽግግር ኪንደርጋርተኖች እና ትምህርት ቤቶች በጋራ  ለማገዝ አብርው እየሰሩ ነው።

ትምህርት ቤት ውስጥ የተርም 1 ትኩርት የሚሆነው በዚህ አመት እንደ ታቀደው የአራት አመት እድሜ ኪንደርጋርተርን በአካል መሄድ ያልቻሉትን ህጻናት ማገዝ ነው።  

ትምህርት ቤቶች የ2021 ፕሬፕ ተማሪዎችን ለማገዝ የተለያዩ ነገሮችን እያደርጉ ነው፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል

 • በመስመር ላይ (ኦንላይን) የትምህርት ቤት እና የመማሪያ ክፍል ጉብኝት
 • ‘የርእሰ መምህሩ መተዋወቂያ’ ቪዲዮዎች
 • ‘የፕሬፕ ቡድኑ መተዋወቂያ’ ቪዲዮ ውይይቶች
 • የኪንደርጋርተን እና ፕሬፕ መምህራን ስብሰባዎች
 • የ5ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፕሬፕ ተማሪዎች ጓደኛ እንዲሆኑ ማሰልጠን

ልጅዎን እስከ አሁን ድርስ ለ2021 ፕሬፕ ካላስመዘግቡ አሁኑኑ ለልጅዎ ትምህርት ቤት እንዲፈልጉ እናበርታታዎታለን። ልጅዎን በተቻለ ፍጥነት ቢያስመዘግቡ የተሻለ ነው። የትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ትምህርት ስለመጀምር በጣም ጠቃሚ መርጃ በድረ ገጻቸው ላይ ይገኛል።

ፕሬፕ በ2021 ምን እንደሚመስል  ለማወቅ ከፈለጉ የልጅዎ ትምህርት ቤት መምህራንን ያነጋግሩ። የልጅዎን ከኪንደርጋርተን ወደ ትምህርት ቤት ሽግግር ለማቀድ የልጅዎ ኪንደርጋርተን መምህር ሊያግዝዎ ይችላሉ።

አስተጓሚ ይፈልጋሉ?

ወደ 9280 1955 በመደወል ወይንም ይህንን ድረ ገጽ በመጎበኝት ኪንደጋርተኑ አስተጓሚ እንዲያዘጋጅልዎ መጠየቅ ይችላሉ።

በጤና እና በደህና ሁኔታ ለመኖር ማድርግ የሚችሉዋቸው ነገሮች (Things you can do to stay healthy and safe)

ቻይልድ ኬሩ ወይንም ኪንደርጋርተኑ የልጅዎን እና የቤተሰብዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚከተሉትን ያደርጋል

 • ህጻናቱ ወደ ማእከሉ ወይንም ኪንደርጋርተኑ ሲደርሱ ሙቀታቸውን በየእለቱ በመለካት
 • ዘወትር ህንጻውን እና መገልገያዎችን በማጽዳት
 • አዋቂዎችን የአፍ እና አፍንጫ መሸፋኛ ጭምብል እንዲያደርጉ በመጠየቅ
 • የጤንነት ሰሜት የማይሰማቸ ህጻናትን ወይንም ቤተሰቦችን እቤታቸው እንዲቀመጡ በማበርታት። በተጨማሪም ለኮሮናቫይርስ (ኮቪድ-19) እንዲመርመሩ በማበርታት።  

እቤትዎ ውስጥ እንዴት ንጽህና መጠበቅ እንደሚቻል ከቤተሰብዎ ጋር ስለሚከተሉት ጉዳዩች እንዲነጋገሩ እንጠይቅዎታለን

 • ወደ ቻይልድ ኬሩ ወይንም ኪንደርጋርተኑ ከመምጣትዎ በፊት እጅን ይታጠቡ ወይንም የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ይጠቀሙ 
 • በማንኛውም ጊዜ ከቤትዎ ሲወጡ የአፍ እና አፍንጫ መሸፋኛ ጭምብል ያድርጉ፣ ይህም ወደ  ቻይልድ ኬሩ ወይንም ኪንደርጋርተኑ  ሲሄዱ ያካትታል
 • አብርዎት ከማይኖሩ ሰዎች ጋር ሲገናኙ የ1.5 ሜትር እርቀት መጠበቅ። ይህም ቻይልድ ኬሩ ወይንም ኪንደርጋርተኑ የሚሰሩ ሰራተኞች ወይንም ሌሎች ቤተሰቦችን ያጠቃልላል። 
 • ሲያስሉ ወይንም ሲያስነጥሱ በንጽህና መጠበቂያ ወርቀት ላይ (ቲሹ) ወይንም ክርንዎን ይጠቀሙ። ከሳሉ ወይንም ካስነጠሱ በኋላ ሁልጊዜ እጅዎን ይታጠቡ።
 • የህመም ስሜት ካለብዎ እቤትዎ ይቀመጡ። የህመም ስሜት ካለብዎ ለኮሮናቫይርስ (ኮቪድ-19) ይመርመሩ። እንደገና የጤንነት ስሜት እስከሚሰማዎት ድርስ እቤትዎ ይቀመጡ።

Reviewed 06 November 2020

24/7 Coronavirus Hotline

If you suspect you may have COVID-19 call the dedicated hotline – open 24 hours, 7 days.

Please keep Triple Zero (000) for emergencies only.

Was this page helpful?