vic_logo
coronavirus.vic.gov.au

ለጤና ምክርና እገዳዎች (Health advice and restrictions) - በአማርኛ (Amharic)

ወቅታዊ የሆነ ለጤና ምክርና እገዳዎች፤ ይህም እንዴት በደህንነት መቆየት እንደሚቻል፤ ምርመራ ማካሄድ እንደሚቻልና ለርስዎ የሚቀርብ ድጋፍ መረጃን ያካተተ ይሆናል።

የሚያሳስብዎት ከሆነ ለኮሮና ቫይረስ/coronavirus በሆትላይን 1800 675 398 (24 ሰዓታት) መደወል።.
አስተርጓሚ ካስፈለግዎት፤ ለ TIS National በስልክ 131 450 መደወል.
እባክዎን በሶስት ዜሮ (000) ለድንገተኛ ችግር ብቻ መደወል.

ማስታወስ ያለብዎት

የቤተሰባችንና የማህበረሰባችንን (COVID-19) ደህንነት ለመጠበቅ ማድረግ የሚገባን ጠቃሚ ነገሮች አሉ።

 • በተደጋጋሚ እጆችዎን መታጠብ። ሳሙና እና ውሃ መጠቀም ወይም የእጅ ማጽጃ/ሳኒታይዘር መያዝ። ይህ በስፍራዎች ላይ ለብዙ ቀናት በህይወት መቆየት ከሚችል ኮሮናቫይረስ (COVID-19) ደህንነታችን እንዲጠበቅ ይረዳናል።
 • ከሌሎች ሰዎች እርቀትን በ 1.5 ሜትር መጠበቅ።
 • ከቤት ሲወጡ ሁልጊዜ የፊት መሸፈኛ ጭንብል መያዝ አለብዎት።
 • ወደ ሆስፒታል ወይም እንክብካቤ መስጫ መገልገያ ለጉብኝት በሚሄዱበት ጊዜ፤ በህዝባዊ ማጓጓዣ ላይ ማለት በታክሲ ወይም በጋራ መጠቀሚያ ተሽከርካሪ (ኡቨር) ውስጥ እና በአየር መንገድና በበረራ ላይ ሲሆኑ (የፊት መሸፈኛ ጭንብል ላለማጥለቅ ህጋዊ ምክንያት እስከሌለ ድረስ) የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማጥለቅ አለብዎት።
 • በሌላ ሁኔታዎች ላይ ማለት ከሌሎች ሰዎች እርቀትን በ1.5 ሜትር መቆየት ካልቻሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብልን ማጥለቁ በጥብቅ ይመከራል። ይህ የኮሮናቫይረስ (COVID-19) ስርጭት መጠን ይቀንሳል።
 • ቤተሰብንና ጓደኞችን በቤት ውስጥ ሳይሆን ከቤት ውጭ ሆኖ መገናኘት። ከቤት ውጭ የሚያዝን ኮሮናቫይረስ (COVID-19) እንዲቀንስ ማድረግ እንችላለን።
 • የህመም ስሜት ካለዎት ምርመራ ማካሄድ እና እቤት መቆየት። ምንም እንኳን ያለዎት የበሽታ ምልክት አነስተኛ ቢሆንም፤ ቀደም ብሎ ምርመራ ማካሄዱ የኮሮናቫይረስ (COVID-19) ስርጭት እንዲቀንስ ያደርጋል።
 • የኮሮናቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለሁሉም ሰው በነጻ ነው። በዚህ የሚካተት የ Medicare card ለሌላቸው ሰዎች እንደ ከውጭ አገር ለመጡ ጎብኚዎች፤ ማይግራንት ሰራተኛችንና የጥገኝነት ጠያቂ ሰዎችን ይሆናል።

በአሁን ጊዜ በቪክቶሪያ ያለው የእገዳ ደረጃ

በቪክቶሪያ ያሉትን ወቅታዊ እገዳዎች ያንብቡ።

ሁኔታዎች ከተቀየረ የቪክቶሪያ ጤና ዋና ሀላፊ/ Victorian Chief Health Officer ያሉትን እገዳዎች መቀየር ይችላል።

ወቅታዊ እገዳዎች

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ:

 • ከቤት ውጭ እስከ 200 ሰዎች መሰብሰብ ይችላሉ። ይህ በውጭ የህዝባዊ ቦታ ላይ መሆን አለበት፤ ይህም እንደ መናፈሻ ቦታ ወይም ባህር ዳርቻ እንጂ – እቤትዎ ውስጥ ሆኖ አይደለም።
 • በቤትዎ በቀን እስከ 100 እንግዶች ሊኖርዎት ይችላል።
 • በቪክቶሪያ ውስጥ የእረፍት እቅድ ካለዎት ከቤተሰብዎ ጋር ሆነው እስከ 100 ሰዎች ለእረፍት መጠለያ ቦታ ማቀናጀት ይችላሉ። በጣም ለሚቀራረቡ የትዳር ጓደኞች እና እድሚያቸው ከ12 ወራት በታች ለሆኑ ህጻናት በ100 ሰዎች ቁጥር ላይ አይካተቱም።
 • ጸጉር አስተካካይ፣ የቁንጅና ሳሎን እና የግላዊ እንክብካቤ ሰጪ አገልግሎቶች እቤትዎ መምጣት ይችላሉ።
 • ምግብ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች እና ካፌዎች ክፍት ናቸው። በውስጥና በውጭ ላይ የደንበኞችን ቁጥር ለመወሰን የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ ተግባራዊ መሆን አለበት። የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት እስከ 25 ደንበኞች ይፈቀዳል።
 • በቁጥር ከተወሰኑ ደንበኞች ጋር ካዚኖዎች ክፍት ናቸው።
 • በአካል የሚቀርብ ሙዚቃ ይፈቀዳል።
 • የምግብ መሸጫ አዳራሾች ክፍት ናቸው።
 • የንክኪ ስፖርቶች በቤት ውስጥ እና በውጭ ሆኖ ይፈቀዳል።
 • ጅምላስቲክና በቤት ውስጥ ሆኖ የአካል እንቅስቃሴ ክፍለ ትምህርት ክፍት ይሆናል። በጅምላስቲክና በቤት ውስጥ የስፖርት መገልገያ ቦታ ላይ የደንበኞችን ቁጥር ለመወሰን የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ/two square metre rule ተግባራዊ መሆን አለበት። ጅምላስቲክ ያለ ሰራተኛ አባል ለማካሄድ በሁለት ካሬ ሜትር ደንብ ተግባራዊ መሆን አለበት።
 • የመዋኛ ገንዳዎች ክፍት ናቸው። በመዋኛ ገንዳ ላይ የደንበኞችን ቁጥር ለመወሰን የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ/two square metre rule ተግባራዊ መሆን አለበት።
 • በቁጥር ከተወሰኑ ደንበኞች ጋር ሲኒማዎች ክፍት ናቸው።
 • ሰርግ መፈጸም ይችላል። ምን ያህል ሰው መገኘት እንደሚችል በቦታው መጠን መሰረት ይሰላል። ይህ ቦታ የሁለት ካሬ ሜትር ደንብያሟላ መሆን አለበት። በቤትዎ ሰርጉን ካካሄዱት እስከ 100 ሰዎች መገኘት ይችላሉ።
 • የቀብር ስነ-ስርዓት ይፈቀዳል። ምን ያህል ሰው መገኘት እንደሚችል በቦታው መጠን መሰረት ይሰላል። ይህ ቦታ የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ ያሟላ መሆን አለበት። የቀብር ስነ-ስርዓት በቤትዎ ካካሄዱት እስከ 100 እንግዶች መገኘት ይችላሉ።
 • ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች መሰባሰብ ተፈቅዷል። ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች መሰባሰብ መገኘት የሚችሉት የሰዎች ቁጥር መጠን የሚሰላው በሁለት ካሬ ሜትር ደንብ ተግባራዊ በማድረግ ነው። በቤት ውስጥ እና በውጭ ማክበር አገልግሎቶች በተመሳሳይ ጊዜ ማካሄድ እንደሚቻልና የቡድን መጠን ገደብ አይኖርም።
 • የማህበረሰብ ቦታዎች፤ ማለት ቤተመጽሀፍትንና የጐረቢታሞች መሰባሰቢያ ማዕከሎች ያካተተ ክፍት ናቸው። በነዚህ ቦታዎች ላይ የሁለት ካሬ ሜትር ደንብ መሰረት የሰዎችን ቁጥር መጠን ተግባራዊ ያደረገ መሆን አለበት።
 • እስከ ቀን 23 ሚያዚያ/April ባለው ግዜ ውስጥ ሁሉም መገልገያ ቦታዎች ኤሌትሮኒካል የመረጃ መዝገብ ሊኖራቸው ይገባል።

የፊት መሸፈኛ ጭምብል

ከቤት ሲወጡ ሁልጊዜ የፊት መሸፈኛ ጭንብል መያዝ አለብዎትና የፊት መሸፈኛ ጭንብል ላለማጥለቅ ህጋዊ የሆነ ምክንያት ከሌለዎት በስተቀር አስፈላጊ ሲሆን ማጥለቅ አለብዎት። ለምሳሌ፡ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ላለማጥለቅ ህጋዊ ምክንያት ውስጥ የሚካተት:

 • የጤና ችግር ካለብዎት፤ ይህም በፊትዎ ላይ እንደ ከባድ የቆዳ ችግር ወይም እንደ የትንፋሽ ችግር ካለብዎት
 • የአካል እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ጊዜ ትንፋሽ ካጠርዎት።

እድሚያቸው ከ12 ዓመት በታች ለሆኑት ህጻናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ አይኖርባቸውም።

ህጋዊ የሆነ ምክንያት ከሌለዎት በስተቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ያለበዎት

 • በህዝብ መጓጓዣ ላይ በሚጓዙበት ጊዜ
 • በሆስፒታል ወይም በእንክብካቤ መስጫ መገልገያ ላይ ጉብኝት በሚያደርጉበት ጊዜ
 • በጋራ መጠቀሚያ ተሽከርካሪ (ኡቨር) ውስጥ በሚሆኑነት ጊዜ
 • በአየር መንገድ እና በበረራ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ይሆናል።

ከሌሎች ሰዎች እርቀትዎን በ1.5 ሜትር መጠበቅ ካልቻሉ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማጥለቅ እንዳለብዎት ይመከራል።

ስለ መመርመርና እራስን ማግለል

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ማንኛውም ምልክት ካለብዎት፤ ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት (get tested) እና የምርመራ ውጤቱን እስኪያገኙ ድረስ ከቤትዎ መቆየት። ወደ ሥራ ወይም መገበያያ ሱቆች ላይ አለመሄድ።

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች የሚያካትቱት:

 • ትኩሳት፣ ብርድ-ብርድ ማለት ወይም ማላብ
 • መሳል ወይም የጉሮሮ ህመም
 • የትንፋሽ ማጠር
 • በአፍንጫ ፈሳሽ
 • የሽታ ወይም መቅመስ ስሜትን ማጣት

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለእያንዳንዱ ሰው ያለክፍያ በነጻ ነው። በዚህ የሚካተት Medicare ካርድ ለሌላቸው ሰዎች፤ ማለት እንደ ከውጭ አገር የመጡ ጎብኝዎች፤ ማይግራንት/መጤ ሰራተኞች እና ለጥገኝነት ጠያቂ ሰዎችን ይሆናል።

ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በምርመራ ከተገኘብዎት፤ እራስዎን ከውሌሎች ሰዎች በክፍልዎ ውስጥ ማግለል አለብዎት። ለበለጠ መረጃ በምርመራ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ከተገኘብዎት ምን ማድረግ አለብዎ የሚለውን (ቃል) ማየት።

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ካለበት የሆነ ሰው ጋር በቅርበት ግንኙነት አድርገው ከሆነ፤ ለ 14 ቀናት በተገልሎ ማቆያ ውስጥ እራስዎን ከሌሎች አገልሎ መቆየት። ለበለጠ መረጃ በምርመራ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ከተገኘብዎት ምን ማድረግ አለብዎ የሚለውን (ቃል) ማየት።

በቅርበት ግንኙነት ከተደረገበት ከሆነ ሰው ጋር አብረው ከነበሩ ወይም ጊዜ ካጠፉ ታዲያ ከሰው ተገልለው እቤት እንዲቆዩ ይጠየቃሉ።

ድጋፍ ይቀርባል

ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ ውጤት እስኪያገኙ ድረስ ባለዎት የገቢ መጠን ማጣት የሚያሳስብዎት ከሆነ፤ ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ካደረጉ በኋል ተገልሎ ለመቆየት የ $450 ለማግኘት ይፈቀድልዎት ይሆናል። ይህ ክፍያ እቤትዎ እንዲቆዩ ለመደገፍ ይረዳዎታል።

በምርመራ ውጤት ከተገኘብዎት ወይም ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት አድርገው ከሆነ፤ የ $1,500 ክፍያ ሊፈቀድልዎ ይችል ይሆናል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ለኮሮና ቫይረስ ሆትላይን መስመር በስልክ 1800 675 398 አድርጎ መደወል። አስተርጓሚ ከፈለጉ ዜሮን (0) ይጫኑ።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት የሆነ ሰው የጭንቀት መንፈስ ካደረበት ወይም አሳሳቢ ጕዳይ ካለዎት በሆት ላይን መስመር በስልክ 13 11 14 ወይም በብዮንድ ብሉ/Beyond Blue በስልክ 1800 512 348 አድርገው መደወል ይችላሉ። አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ መጀመሪያ በስልክ 131 450 መደወል።

የመገለል ስሜት ካደረብዎት የኮሮና ቫይረስ ሆትላይን መስመር (Coronavirus Hotline) በስልክ 1800 675 398 አድርጎ መደወልና ቁጥር ሶስትን (3) መጫን። አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ ዜሮን (0) መጫን። ከዚያ ከአካባቢ ድጋፍ አገልግሎቶች ጋር ማገናኘት ከሚችል የAustralian Red Cross ፈቃደኛ ሰራተኛ ጋር ያገናኝዎታል።

መገልገያ ምንጮች

እባክዎን ከታች የተዘረዘሩትን ቁሳቁሶች ይጠቀሙ እንዲሁም ለማሀበረሰብዎ በኢሜል፣ በማህበራዊ መገናኛዎች ወይም በማህበራዊ መረቦች ያካፍሉ።

ምርመራ ማካሄድና ከሌሎች ተገልሎ መቆየት

በደህንነት መቆየት

እርዳታ ስለማግኘት

የፊት መሸፈኛ

Reviewed 31 March 2021

24/7 Coronavirus Hotline

If you suspect you may have coronavirus (COVID-19) call the dedicated hotline – open 24 hours, 7 days.

Please keep Triple Zero (000) for emergencies only.

Was this page helpful?