vic_logo
coronavirus.vic.gov.au

ደህንነት (Safety) - አማርኛ (Amharic)

በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅት እርስዎ እና ቤተሰብዎ ደህንነትዎ የተጠበቀ ሆኖ ለመቆየት የሚረዳ መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ በኮሮናቫይረስ (COVID-19) ቪክቶሪያ ድረ ገጽ [Coronavirus (COVID-19) Victoria homepage] ላይ ማግኘት ይችላሉ። 

በቋንቋዎ የበለጠ እገዛ ከፈለጉ በTIS National በ131 450 በመደወል አስተርጓሚ መጠየቅ ይችላሉ ፣ ከዚያም በ13 22 15 ከቢዝነስ ቪክቶሪያ ጋር ለመገናኘት መጠየቅ ይችላሉ።

የቤተሰብ ዓመፅን ማምለጥ (Escaping family violence)

ምንም እንኳን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሰዓት እላፊ ገደብ የተደነገገ ቢሆንም፣ ከቤት ውስጥ ጥቃት ለማምለጥና እርዳታ ለማግኘት በማንኛውም ሰዓት   ከቤትዎ መውጣት ይችላሉ። ምንም ቅጣት አይጣልብዎትም። በዚህ ጊዜ ፖሊስ ካስቆመዎት እቤትዎ ችግር እንዳለና ቤት ውስጥ ደህንነት እንደማይሰማዎ ከነገሩዋቸው ፖሊሶቹ ይረዱዎታል። ወደ ሦስት ዜሮ (000)) ይደውሉ ወይንም በቀን 24 ሰዓትና በሳምንት 7 ቀናት አገልግሎት በሚሰጠው ሴፍ ስቴፕስን (safe steps) በስልክ 1800 015 188 ወይንም  በኢሜይል safesteps@safesteps.org.au ወይንም ድረ ገጻቸው www.safesteps.org.au/chat ላይ ውይይት (webchat) ይክፈቱ።

ለቤተሰብ ሁከት ፈጠራ ድጋፍ – በመንግሥት መኖሪያ ቤት ህንጻዎች (Family violence support – public housing estates)

እርስዎ ወይም ልጆችዎ በቤትዎ የደህንነት ስሜት ከሌለ ወይም የሚፈሩ ከሆነ እርዳታ ይቀርባል። በደህንነት ማጣት ምክንያት እቤትዎ መውጣት ካስፈለግዎት ከፖሊስ ጋር ችግር እንደማይኖርዎ ወይም ቅጣት እንደማያገኙ ነው።

ለርስዎ ደህንነትና ለልጆችዎ ደህንነት ቅድሚያ እንሰጣለን።

በቀጥታ አደጋ ላይ ካሉ በሶስት ዜሮ (000) ይደውሉ።

ደህና ካልሆኑ ከርስዎ ቤት/ፍላት መውጣት እንደሚችሉና ወደ መሬት ባለው ፎቅ ወለል ላይ በመሄድ እርዳት መፈለግ። ለጤና ጥበቃ ሰራተኛ፤ ፖሊስ ወይም ለሌላ ድጋፍ ሰራተኛ ማነጋገር እንደሚችሉና ሊረድዎት ይችላሉ።

ያለዎት ቪዛ ምንም ችግር አይፈጥርም፤ እዚህ ላይ የሚቀርበው አገልግሎት እርስዎን ማዳመጥና የሚፈልጉት እርዳታ ካለ ማቅረብ ይሆናል።

በተከራይና አከራ ውል ስምምነት ላይ ባይመዘገቡም ችግር የለውም – እርዳታውን ግን ያገኛሉ።   ስለርስዎ ተከራይና አከራ ውል ያለው ሁኔታ መረጃ ለሌላ አውጥቶ አይሰጥም።

መርዳት የሚችሉ አገልግሎቶች

የቤተሰብ ሁከት ፈጠራና ዝምድና ግኝኙነት ምክር

በስልክ ወይም ኢንተርኔት በመጠቀም ስለ ደህንነት መነጋገር ከቻሉ፤ እንዲሁም ከልዩ ባለሙያ የቤተሰብ ሁከት ፈጠራ አገልግሎቶች እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። ለአስተርጓሚ መጀመሪያ ለTIS በስልክ 131 450 መደወል

safesteps  በስልክ  1800 015 188 (በቀን 24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት) መደወል።. እንዲሁም ኢሜል ማድረግ ይችላሉ፤ safesteps@safesteps.org.au ወይም በድረገጽ መስመር ላይ ለቤተሰብ ሁከት ፈጠራ ላይቭ ወብ ቻት/Live Web Chat

InTouch በስልክ 1800 755 988 መደወል። በማይግራንት/መጤና ስደተኛ ለመጡ ሴቶች፤ በቪክቶሪያ ውስጥ ላሉ ቤተሰባቸውና ማህበረሰባቸው በልዩ ባለሙያ የቤተሰብ ሁከት ፈጠራ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።

1800RESPECT በስልክ 1800 737 732 (በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት ለ 7 ቀናት) መደወል። በቤተሰብ ሁከት በወሲባዊ ጥቃት ለተቸገሩ ሚስጢራዊ የሆነ መረጃ፤ መማክርት እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።

w/respect (LGBTIQA communities) በስልክ 1800 542 847 (ከጥዋቱ 9.00 am እስከ ከሰዓት በኋላ 5.00 pm ከሰኞ እስከ ዓርብ፤ እንዲሁም ከሥራ ሰዓት ውጭ ድጋፍ ሁልጊዜ ረቡእ እስከ ምሽቱ 11.00 pm ሲቀርብ ቅዳሜና እሁድ ከጥዋቱ  10.00 am እስከ ምሽቱ 10.00 pm እርዳታ ይቀርባል)። ስለጤናማ ዝምድና ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ መገልገያ ምንጮችን፤ ጠቃሚ ምክሮችን ያቀርባሉ፤ እንዲሁም በቤተሰብ ሁከት ጥቃት ለደረሰባቸው ድጋፍን ያቀርባሉ።

ወሲባዊ ጥቃት

Sexual Assault Crisis Line በስልክ 1800 806 292 (በቀን 24 ሰዓታት በሳምንት 7 ቀናት)) መደወል ወይም በኦንላይን መስመር እነሱን ማነጋገር Sexual Assault Crisis Line – contact us

ለአቦርጂናል እና ቶረስ አይላንደርስ ድጋፍ

Djirra በስልክ 1800 105 303 መደወል በኢሜል info@djirra.org.au ወይም በድረገጽ ለማየት facebook.com/DjirraVIC

VACCA Preston – 9287 8880, Dandenong – 9108 3500, Werribee - 9742 8300 ወይም በኢሜል vacca@vacca.org ወይም በድረገጽ ለማየት facebook.com/vaccaorg

ለወጣቶች ድጋፍ

Kids Helpline – በስልክ 1800 55 1800 (በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት ለ 7 ቀናት) መደወል። ግላዊና ሚስጢራዊነት ባለው የሙሉ ቀን 24/7 እና በኦንላይን መስመር ላይ የመማክርት አገልግሎት ከ 5 እስከ 25 ዓመት እድሜ ላሉ ወጣቶች ይቀርብላቸዋል።.

በደህንነት ለመቆየት ሌላ ዘዴዎች

  • የ coronavirus (COVID-19) ስርጭትን ለመቀነስ እንዲረዳ እቤትዎ ተገልለው በሚቆዩበት ጊዜ እርዳታን ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል
  • እርዳታ ከፈለጉ ወይም ለፖሊስ መደወል ከፈለጉ፤ ለሚያምኑት የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ በሚጠቀሙበት ቃላት ወይም ምልክቶች አድርጎ መናገር። ለምሳሌ፡ ለጓደኛ ‘ወተት ይፈልጋሉን?’ በማለት ይህም በሚፈልጉት የምልክት እርዳታ በማሳየት መሆን አለበት
  • ቶሎ ብሎ ለመውጣት ወይም ለፍርሃት ስሜት የታቀደ ምክንያት። ለምሳሌው፡ ‘Sarah ወተት እንድወስድላት ትፈልገኛለች።
  • የሁከት ፈጠራ ጸባይ እየባሰ ከመጣ ወይም ብዙጊዜ በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ፤ እርዳታ መፈለጉ ጠቃሚ ነው።
  • ቦርሳን ከቅያሬ ልብሶች ጋር፤ ገንዘብን እና ማንኛውም ተደብቆ የነበሩትን ጠቃሚ የሆኑትን ሰነዶች ምናልባት ከቤት በፍጥነት መውጣት ካለብዎት አዘጋጅቶ መጠበቅ

ሁከት ለተጠቀሙ ወንዶች ሊረዱ በሚችሉ አገልግሎቶች ላይ የሚካተት:

Men’s Referral Service ማነጋገር የሚቻለው በየቀኑ ለ 24 ሰዓታት በስልክ 1300 766 491 መደወል

Dardi Munwurro ለአቦርጅናል ወንዶች እርዳታ እንደሚቀርብ እና በቀን ለ 24 ሰዓታት በተለፎን መስመር – 1800 435 799 ላይ ይቀርባል።

ግብአቶች (Resources)

ለቤተሰብ ሁከት ፈጠራ ድጋፍ – በመንግሥት መኖሪያ ቤት ህንጻዎች - አማርኛ - Family violence support – public housing estates (Word)

Reviewed 19 November 2020

24/7 Coronavirus Hotline

If you suspect you may have COVID-19 call the dedicated hotline – open 24 hours, 7 days.

Please keep Triple Zero (000) for emergencies only.

Was this page helpful?