vic_logo
coronavirus.vic.gov.au

ጉዞ እና መጓጓዣ (Travel and transport) - አማርኛ (Amharic)

በሕዝብ ማመላለሻ ፣ በለይቶ ማቆያ፣ ከኣንዱ መንግስታዊ ኣስተዳደር ወደ ሌላው መንግስታዊ ኣስተዳደር እንዲሁም ከአገር ውጪ በሚደረጉ ጉዞዎች ስለተደረጉ ለውጦች በመከታተል ይወቁ።

በቋንቋዎ የበለጠ እገዛ ከፈለጉ በTIS National በ131 450 በመደወል አስተርጓሚ መጠየቅ ይችላሉ፣ ከዚያም በ1800 800 007 ከህዝብ ትራንስፖርት ቪክቶሪያ የጥሪ ማዕከል ጋር እንዲገናኙ ይጠይቁ።

ወቅታዊ የጉዞ መረጃ

ከማክሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2021 ከሌሊቱ 11፡59 ጀምሮ ከቀይ ዞን ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ካሰቡ፣ እባክዎ ይህን ልብ ይበሉ፦

 • ዋናው የጤና መኮንን (Chief Health Officer) የቀይ ዞን ፈቃድ መስጠትን ለጊዜው አቁሟል።
 • ከማክሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2021 ከምሽቱ 11:59 በኋላ ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ከፈለጉ እና ከመግባትዎ በፊት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ በቀይ ዞን ውስጥ ከሆኑ ለመግባት ነፃ፣ ልዩ ወይም ብቁ ፈቃድ ያስፈልግዎታል። ይህ ለቪክቶሪያ ነዋሪዎችም ይሠራል።

  • ከእገዳ ነፃ የመሆን ፈቃዶች፦ ከእገዳ ነፃ ለመሆን ማመልከት አለብዎት። ከእገዳ ነፃ የመሆን ፈቃዶች የሚሰጡት እንክብካቤ እና ርህራሄ ጋር የተገናኙ ምክንያቶች ያላቸውን ጨምሮ በልዩ ሁኔታዎች ብቻ ነው።

  • ልዩ ሁኔታዎች፦ ልዩ ሁኔታ ለየት ያሉ ምድቦችን ብቻ ይመለከታሉ (ለምሳሌ ለአየር መንገድ ሠራተኞች፣ ወይም በአደጋ ጊዜ የሚጓዙ ከሆነ ወይም ከጉዳት ለማምለጥ የሚጓዙ ከሆነ)።

  • መሥፈርቱን የሚያሟሉ ፈቃዶች፦ መሥፈርቱን የሚያሟሉ ፈቃዶች በቪክቶሪያ በኩል ወደ ሌላ ክልል ለሚጓዙ ሰዎች እንዲሁም የመተላለፊያ ፈቃዶችን እና በውል በሚታወቅ የሠራተኞች ፈቃድ ላይ ስማቸው ተለይተው የተዘረዘሩ የሠራተኞች ፈቃዶችን ያካትታሉ።

 • ከእገዳ ነፃ የመሆን ፈቃድ፣ ያለ ልዩ ወይም ብቁ የሆነ ፈቃድ ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ከሞከሩ፣ 5452 የአወስትራሊያ ዶላር ይቀጣሉ ብሎም ለመግባት ሊከለከሉ ይችላሉ፣ ወይም በራስዎ ወጪ ለ 14 ቀናት በሆቴል ተገልለው (በኳራንቲን) እንዲቀመጡ ይደረጋል።

 • ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ የሚተላለፉ ተጓዥ ከሆኑ፣ እባክዎ በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኝ እንዳለ ያስተውሉ። በኒው ሳውዝ ዌልስ የጤና መምሪያ በማህበረሰቡ በከፍተኛ ደረጃ በሽታው ይተላለፍባቸዋል ተብለው በግሬተር ሲድኒ በተለዩ አካባቢዎች በኩል ከመተላለፍ መቆጠብ አለብዎት። በእነዚህ አካባቢዎች የግድ መጓጓዝ/መተላለፍ ካለብዎት፣ በተቻለ መጠን በእነዚህ አካባቢዎች ለነዳጅ፣ ለምግብ ወይም ለእረፍት እንዳያቆሙ ለማድረግ ጉዞዎን አስቀድመው ማቀድ አለብዎ።

በአውስትራሊያ እና በኒውዚላንድ ስላለው ወቅታዊ ቀይ፣ ብርቱካናማ እና አረንጓዴ ዞኖች መረጃን ለመመልከት፣ ወቅታዊ የጉዞ መረጃ ገጽ ይጎብኙ።

ለቪክቶሪያ ነዋሪዎች የጉዞ ፈቃድ አሰራር (Victorian Travel Permit Scheme) 

ከየትኛውም የአውስትራሊያ እና የኒውዚላንድ አከባቢ ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ያስፈልግዎታል።

የፈቃድ አሰራሩ ለቪክቶሪያ ነዋሪዎች ሲሆን ከሌላ አስተዳደር ክልል ወደ ቤታቸው ለሚመለሱት ነው።

ቪክቶሪያ ሌሎች የአውስትራሊያ እና የኒውዚላንድ አከባቢዎችን በአካባቢው ባለው የኮሮና ቫይረስ አደጋ ላይ በመመርኮዝ አረንጓዴ፣ ብርቱካናማ ወይም ቀይ በማለት ይመድባል፡፡

ፈቃድ ለማመልከት ስለርስዎ ዝርዝር መረጃ ማለት ከየት እንደሚመጡ እና ወዴት እንደሚጓዙ ማቅረብ ይኖርብዎታል።

በድንበር ላይ ላሉ ማህበረሰቦች የሚኖሩ ሰዎች ፈቃድ ማውጣት አያስፈልጋቸውም ነገር ግን በድንበር መካከል ስለመኖራቸው የሚያሳይ የቤት አድራሻን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል:

ለፈቃድ በአገልግሎት ቪክቶሪያ በኩል አድርጎ ማመልከት

የፈቃድ ዞኖች

ቀይ ዞን ማለት የቪክቶሪያ ነዋሪ ካልሆኑ በስተቀር ወደ ቪክቶሪያ መግባት አይችሉም ማለት ነው፡፡ የቪክቶሪያ ነዋሪ ሆነው ከቀይ ዞን ወደ ቪክቶሪያ የሚገቡ ከሆነ በቤት ውስጥ ለ14 ቀናት ለብቻዎ መለየት ይኖርብዎታል፡፡ ለመግባት አንዳንድ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ እንደ  Specified Worker ወይም Freight Workers ፈቃድ ያለው ወይም  በርህራሄ ምክንያት የሚሰጥ ለየት ያለ ፈቃድ  ሲኖር። ያለ ልዩ ፈቃድ ወይም የስራ ፈቃድ ከቀይ ዞን ከመጡ፣ በገንዘብ ተቀጥተው ወደመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል።

ቢጫ ዞን ማለት ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ፈቃድ ማመልከት እንደሚችሉ እና ቪክቶሪያ ከደረሱ በ 72 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ያደርጋሉ። ምርመራዉን ከማድረግ በፊትና በኋላ  ከቫይረስ ነጻ የሆነ ምርመራ ውጤት እስኪያገኙ ድረስ እቤትዎ መቆየት አለብዎት።

አረንጓዴ ዞን ማለት ወደ ቪክቶሪያ ለመግባት ፈቃድ ማመልከት እንደሚችሉና መግባት እንደሚችሉ ነው። አንዴ ወደ ቪክቶሪያ ከገቡ በኋላ ለበሽያ ምልክቶች መከታተል እንዳለብዎትና ካመምዎት ምርመራ ማካሄድ አለብዎት።  

በአውስትራሊያ እና በኒውዚላንድ ውስጥ ያሉ ቀይ ፣ ብርቱካናማ ወይም አረንጓዴ ዞኖች ለማየት በቪክቶሪያ የጉዞ ፈቃድ ስርዓት ገጽ ​​(the Victorian Travel Permit System page) ላይ ያለውን ካርታ ይመልከቱ ፡፡

ከፈቃድ ማውጣት ነጻ መሆን

ተገቢ የሆነ  ምንክንያት ካለዎት ከፈቃድ ነጻ ለመሆን ማመልከት ይችላሉ። በዚ ውስጥ ሊካተት የሚችለው:

 • በህይወት መጨረሻ የሃዘን ድርጊት ወይም የቀብር ስነ-ስርዓት
 • ከጤና፣ ከደህንነት፣ እንክብካቤ ወይም በርህራሄ መንገድ ከሚንከባከቡት ወደ ቤት ስለመመለስ
 • በድንገተኛ ችግር ወደ ሌላ ቦታ መስፈር 
 • በሌላው የድንበር በኩል ላይ ላሉ እንስሳት ደህንነት

Reviewed 23 July 2021

24/7 Coronavirus Hotline

If you suspect you may have COVID-19 call the dedicated hotline – open 24 hours, 7 days.

Please keep Triple Zero (000) for emergencies only.

Was this page helpful?