አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ የትርጉም እና አስተርጓሚ አገልግሎትን በ 131 450 ይደውሉ።
ለምንድን ነው መከተብ ያለብዎት?
ክትባቶች ሰዎች በኮቪድ-19 በጣም እንዳይታመሙ ለመከላከል ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ ናቸው። ከፍተኛውን ከቫይረሱ የመከላከል አቅም እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ክትባቶችን በወቅቱ መውሰድ አስፈላጊ ነው።
እንዴት መከተብ እንደሚቻል
ክትባቶች በነዚህ ስፍራዎች ይገኛል፦
- ሃኪሞች
- የመተንፈሻ ክሊኒክ
- ፋርማሲዎች
- የማህበረሰብ ጤና አገልግሎቶች።
ቀደም ሲል የነበሩ ሁኔታዎች ካሉዎት ወይም ምን ያህል መጠን እንደሚፈልጉ እርግጠኛ ካልሆኑ ሃኪም (GP) ማነጋገር አለብዎት።
ክትባቶች ነጻ ናቸው፣ እና ለመከተብ የሜዲኬር ካርድ አያስፈልግዎትም።
ማን ሊከተብ ይችላል
እድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ ለክትባት ብቁ ናቸው። ከ6 ወር ጀምሮ እና ከ 5 አመት በታች የሆኑ አንዳንድ ልጆች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ካሉባዋቸው ለክትባት ብቁ ይሆናሉ፦
- በሽታ የመቋቋም አቅማቸው የተዳከመ ከሆኑ
- የአካል ጉዳት ካለባቸው
- በርካታ የጤና ችግሮች ካሉባቸው።
የኦምሪኮን (Omicron) ዝርያዎች ያነጣጠረ አዲስ የባይቫለንት ክትባት እድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ እንደ ማበረታቻ/ተጨማሪ መጠን ይገኛል።
ምን ያህል መጠን እና የትኛው ክትባት ለእርስዎ እና ለልጅዎ እንደሚመከር ለማወቅ ሃኪም (GP) ያነጋግሩ። ለበለጠ መረጃ፣ ክትባቱን የሚለውን ይጎብኙ።
ከክትባትዎ በኋላ
መርፌው በተወጉበት ቦታ ህመም፣ ድካም፣ የጡንቻ ህመም፣ ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት እና የመገጣጠሚያ ህመም ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊኖሩብዎት ይችላሉ። የጎንዮሽ ጉዳቶች የተለመዱ መሆናቸውና እና ክትባቱ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው። ብዙውን ጊዜ መለስተኛ መሆናቸውና ከአንድ ወይም ከሁለት ቀን በኋላ ይለቃሉ።
ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ከተጨነቁ ወይም ማንኛውም የጎንዮሽ ጉዳቶች ከጥቂት ቀናት በኋላ ካልጠፉ ዶክተርዎን ያነጋግሩ።
ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች
ሁሉም ክትባቶች በአውስትራሊያ ውስጥ ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በአውስትራሊያ ቴራፒዩቲክ እቃዎች የተቀመጡ ጥብቅ የደህንነት መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። የሚሰጡት ብቃት ባላቸው የጤና ባለሙያዎች ነው።
በአውስትራሊያ ውስጥ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ፈቃድ የተሰጣቸው 4 ክትባቶች ይገኛሉ፣ እነዚህም፡-
- ፋይዘር (Pfizer)
- ሞደርና (Moderna)
- ኖቫቫክስ (Novavax)
- አስትራዘኒካ (AstraZeneca)
ሰዎች በእድሜያቸው እና በጤና ሁኔታቸው ላይ በመመስረት የተለያዩ ክትባቶችን ሊወስዱ ይችላሉ። የትኛው ክትባት ለእርስዎ ትክክል እንደሆነ ለማወቅ ሃኪም (GP) ጋር ይነጋገሩ።
ለተጨማሪ መረጃ
የክትባት ክሊኒክ በመጠቀም የሚቀጥለውን የክትባት መጠንዎን ለመከተብ ሃኪም (GP) ጋር ወይም አከባቢ ፋርማሲ ጋር ቀጠሮ ያስይዙ። ለበለጠ መረጃ፡ ብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ የእርዳታ መስመርን በ 1800 020 080 ይደውሉ።
Reviewed 09 December 2022